Creatorry.Music
ОткрытьПриложение
Heart break
Неизвестный исполнитель•5 месяцев назад

Heart break

en • 4:15

Создать песню
Heart break
Неизвестный исполнитель
•5 месяцев назад

Heart break

en • 4:15

0:004:15
Создать песнюСоздать

Текст песни

ቃላት ስንቅ ሆኖ ሲከፋው መለያየት ያለፉ ትዝታዎች የገፉት ዕውነት ❛❛መለያየት ሞት ነው❜❜ ብላኝ እንዳልነበር ይኀው ተለያየን ሞታ ስትቀበር አፈር ስትለብስ መሬት ሲደብቃት የአዳም ዘር እዳ ከቅፌ ሲነጥቃት ጩኀት ለቅሶ ዋይታ አጅቧት ስጠፋ ነፍስ ይማር የሚል ቃል ጆሮ ላይ ሲከፋ ሞታ ስትቀበር ❛❛መለያየት ሞት ነው ሞት መለያየት ነው❜❜ ብላኝ እንዳልነበር ይኀው ተለየቺኝ አፈር ስትለብስ እንባም አይበቃኝም ላንቺ በምን ላልቅስ የቀብርሽ እለት በልብሰተ ክህኖ ገፁን ያሳመረ ጠይም ደርባባ ቄስ ስለ ሞትሽ ትርጉም እንዲ ተናገረ ❛❛ተው አይለቀስም ምን ሰራህ ተብሎ እግዜር ይወቀሳል አፈር የተጫማ ሊበሰብስ እንጂ ተጉዞ የት ይደርሳል ህያው ልትሆን እንጂ ከፈራሽ ገላዋ ነፍሷን የነጠቀ ያልሞተ አያፈራም ዘር ሆኖ ያልወደቀ❜❜ ተዝካሯን አውጡላት ነድያን መግቡ እሱ እንደው ሩህሩህ አይጨክንም ልቡ ብለው ቢናገሩ ከበደኝ ቀብሩ በመሞት ከሆነ ህይወት የሚጀመር ውልደትሽ ምን ነበር? አንቺስ ፍቅርዬ ❛❛መለያየት ሞት ነው❜❜ ብለሺኝ አልነበር ከኔ ተለይተሽ ጀነት ብትገቢ ብትቆሚ በቀኙ ያንቺን እጣ ማግኘት ሙታን እዲመኙ ወይ ሲኦል ተጥለሽ እልፍ ብትቀጪ ልትወጪ ፀፀት ከልብሽ ብታምጪ ሞታ ስትቀበር ❛❛መለያየት ሞት ነው ሞት መለያየት ነው❜❜ ብላኝ እንዳልነበር ይኀው ተለየቺኝ አፈር ስትለብስ እንባም አይበቃኝም ላንቺ በምን ላልቅስ ስለመለየትሽ እንባ እያፈሰሱ እኔም ከንቱ አፍቃሪሽ ሞት ህያውነት ነው ብዬ እያመንኩ የሞትሽን ትርጉም ከእንባ ላይ አየሁት የሚተን እንደ ጉም...

Heart break

Heart break

Неизвестный исполнитель

0:004:15